No products in the cart.
መኝታ ቤትዎ እንደ ቅዱስ ቦታዎ ነው፡፡ የቀኑን ውጣ ውረድ አረፍ ብለው የሚያጠነጥኑበት ቦታ... ይሄን ቦታ ምቹ እና ሳቢ ለማድረግ የእንቅልፍ ሰዓትዎን የሰላም እረፍት ለማድረግ ትክክለኛ የፈርኒቸር መገልገያ አማራጮችን መጠቀም የግድ ይሆንብዎታል፡፡ እንደ ፍላጎትዎ እና ምርጫዎ የማንበቢያ ጠረጴዛ፣ በርኩማዎች፣ እና ዴስክም በመኝታ ቤትዎ መገልገያዎች ሊያካትቱ ይችላሉ፡፡ ዘወትር ለምርጫ ሲወጡ ሊያስቀድሙት የሚገባው ነገር ግን ጥራት ነው፡፡ በተለይ ከትራሶችዎ እና አልጋ ልብሶችዎ ጋር ልክክ ብሎ ለወገብዎ እና ለትራስዎ ድጋፍ የሚሆን የምቾት አልጋን ይምረጡ፡፡ ጥራትም ላይ አይደራደሩ፡፡ ጥራትን ከውብትና ምቾት ያጣመሩትን እኛ ዘንድ ይሸምቱ፡፡ እንቅልፍ የሰመረ እንዲሆን መኝታዎን ያዘምኑ፡፡ በመኝታቤት መገልገያዎች ላይ ሌላ በትኩረት ልብ ሊሉት የሚገባው ጉዳይ ዕቃ ማስቀመጫ ( ስቶሬጅ) ነው፡፡ ዕቃዎችዎ የያዟቸውን መሳቢያዎች፣ ማንጠልጠያዎች፣ ማስቀመጫዎች በትኩረት ይመልከቱ፡፡ ንብረቶችዎትን፣ ልብስዎትን፣ ዶክመንትና መሰል ነገሮችን በአጋግባቡ ሰብስበው ሊይዙልዎት ስለመቻላቸው ይመርምሩ፡፡ በመጨረሻ የሚገዙት የመኝታ ቤት መገልገያ ከእርስዎ የስታይል ፍላጎት ጋር ሊሄድ ስለመቻሉ በትኩረት ይመልከቱ፡፡ ፍላጎትዎ ምን ዓይነት ቅጥ ወይም ስታይል ያላቸው መገልጌዎችን መጠቀም ነው? ዘመናዊ፣ ባህላዊ፣ ከቀለም እንዲሁም የመኝታ ክፍልዎ ከሚፈልገው ስልት ጋር አብሮ ሊሄድ ስለመቻሉ እና ስለመሳሰለው በቅድሚያ በትኩረት ያጥኑ፡፡ ዋናው ዓላማው ለእርስዎ ምቾትና የመንፈስ እረፍት የሚስማማ የመኝታ ቤት ከባቢ መፍጠር አይደለምን?