No products in the cart.
የመመገቢያ ክፍሎች ቤተሰቦች ወዳጆች፣ የተለዩ አጋጣሚዎችን የሚያከብሩባቸው፣ ውድ ጊዜ የሚያሳልፉባቸው የሚሰባሰቡባቸው ክፍሎች ናቸው፡፡ እናም ሳቢና መሳጭ የእርስዎን ምርጫ እና ንቃት የሚያሳይ የመመገቢያ ክፍል ለመገንባት ትክክለኛውን የፈርኒቸር አማራጭ መምረጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ለመመገቢያ ክፍል መገልገያ ፈርኒቸሮች በርካታ አማራጮች አሉ፡፡ ጠረጴዛዎች፣ ወንበሮች፣ የቡፌ ጠረጴዛዎች፣ የቻይናዊያን ካቢኔቶች የመሳሰሉት... እንደምርጫዎት ለመመገቢያ ክፍልዎት የወይን መደርደሪያ፣ የቀለማት ብርሃን ሊጨምሩበት ይችላሉ፡፡ ምቾት እዚህም ቀዳሚ ነገር ነው፡፡ የሚጋብዟቸውም እንግዶች ዘና ብለው መመገብ ይቻላቸው ዘንድ የሚመርጧቸው መቀመጫዎች ምቹ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ሲቀመጡባቸው ለጀርባዎ እና ለእግርዎ ምቾት የሚሰጡ መቀመጫዎችን ይምረጡ፡፡ ከምቾት ቀጥሎ ሌላው የመመገቢያ ክፍሎች የፈርኒቸር መገልገያዎችን ሲገዙ ልብ ሊሉት የሚገባው ነገር አገልግሎት ነው፡፡ የሚገዙት የመመገቢያ ቤት ዕቃ የእርስዎንና የእንግዶችዎን ፍላጎት ያማከለ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ለምሳሌ የመመገቢያ ጠረጴዛዎት ስፋት እና ጥንካሬ ከክፍልዎና ከፍላጎትዎ ጋር የሚመጣጠን ሊሆን ይገባዋል፡፡ የቡፌ ጠረጴዛዎም የሚያስተናግዷቸውን እንግዶች ያህል የምግብ አቅርቦት የመሸከም አቅም ስለመያዙ እርግጠኛ መሆን ይኖርብዎታል፡፡ በመጨረሻም የሚገዙት የመመገቢያ ቤት ፈርኒቸር የመመገቢያ ክፍልዎን ስፋት እና ቅርጽ ያማከለ ስለመሆኑ በቅጡ ሊያስቡበት ይገባል፡፡ የሚጥፈርልዎ ድባብ አባባይ፣ ተቀባይ፣ መሳጭ ድባብ ስለመሆኑ ሊያስቡበት ይገባል፡፡ ለምርጫዎ የሚቀርቡ በርካታ የመመገቢያ ቤት ጠረጴዛዎች ስላሉ በጥንቃቄ ይምረጡ፡፡ ዋናው የሚፈልጉትን እና ቤትዎ መቀበል የሚችለውን ቤትዎን ማስዋብ ማስጌጥ የሚችለውን ዓይነት ፈርኒቸር ውብ ቅንጡ እና ጠንካራ ፈርኒቸር መምረጥ ነው ጥበቡ፡፡ በብልሃት ከቀረቡት ለእርስዎ የሚሆን አማራጭ መፈለግ ፈታኝ አይደለም፡፡ ይጎብኙን! ምርጫዎን የሚያሟሉትን እኛ ዘንድ ያገኛሉ!