ቢሮዎ የስራ ቦታዎ ነው፡፡ በዕለት ውሎዎ አብዛኛውን ጊዜዎን የሚያሳልፉት እዚያ ነው፡፡ እናም ለዚህ ቦታ የሚመጥኑ ዘመናዊ የፈርኒቸር መገልገያዎችን መምረጥ እና መጠቀም ግዴታዎ ይሆናል፡፡ ለቢሮዎ ውበት እና ምቾት ልዩነት የሚፈጥሩ መገልገያዎችን ይምረጡ፡፡ የቢሮ መገልገያዎች ባለመሳቢያ ጠረጴዛዎችን፣ ወንበሮችን፣ የፋይል እና የመጻሐፍት መደርደሪያዎችንና የመሳሰሉትን ያካትታሉ፡፡ እንደ ምርጫዎ እና ፍላጎትዎ የእንግዳ መቀበያ እና የቡና መጠጫ መገልገያዎችንም ሊያካትቱበት ይችላሉ፡፡ ልክ እንደ ሌሎች የፈርኒቸር መገልገያ ዓይነቶች ሁሉ የቢሮ መገልገያዎችንም በመምረጥ ሂደት ልብ ሊሉት የሚገባው ዋነኛው ጉዳይ ምቾት ነው፡፡ በቢሮዎ ውስጥ ጉዳዮችን ለመጨረስ፣ ደንበኞችን ለማስተናገድ ብዙ ሠዓት የሚቀመጡ ከሆነ የግዴታ ወገብዎንና አንገትዎን ደገፍ የሚያደርጉ መገልገያዎችን መምረጥ ይኖርብዎታል፡፡ ለእርስዎ አካል እና ለቢሮዎ ሁኔታ እንዲሁም ከሚጠቀሙበት ዴስክ ጋር አብሮ የሚሄደውን ወንበር ይምረጡ፡፡ ዴስክዎ ልከኛ የሆነ ቁመት ያለውና ለምንሸራሸር የሚያመች፣ ለጆምፒውተር እና ፋይል አያያዝ በቂ ቦታ ያለው ሊሆን ይገባዋል፡፡ ሌላው የቢሮ መገልገያዎችን በመምረጥ ሂደት ልብ ሊሉት የሚገባው ጉዳይ አገልግሎት ነው፡፡ ቢሮዎ ስራውን ለመከወን ምቹ ሊሆን ይገባዋል፡፡ የቢሮ የፈርኒቸር መገልገያዎችን በሚሸምቱበት ወቅት ስራዎን ለማቀላጠፍ ፋይልዎን ሸክፎ ለመያዝ ምቹ ማስቀመጫዎች ያሏቸውን ይምረጡ፡፡ በመጨረሻ ስታይላቸው ከቢሮዎ ቅጥ ጋር ሊስማማ ስለመቻሉ ያስቡበት፡፡ ቢሮዎ በደንበኞችዎ ፊት የእርስዎን የምርጫ አቅም እና ስራን በቀላሉ የማስኬድ ብቃት የሚያሳይ አንድ መገለጫ ሆኖ ይቀርባል፡፡ ለዚህም ለምርጫዎ የመሆኑ በርካታ ዓይነት አማራጮች እና ዘንድ አሉልዎት፡፡ ዞሮዞሮ ዋናው ነገር አካልዎ ሳይጎዳ፣ ደንበኞችዎ ሳይጉላሉ ወጭ ቆጣቢ እና ሳቢ በሆነ ከባቢ ሥራዎን ለማቀላጠፍ የሚያስችሉዎትን ፈርኒቸሮች መምረጥ መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡ እናም ሲመርጡ ወደ እኛ ይምጡ፡፡ ከሕልምዎ እናስማማዎታልን፡፡