No products in the cart.
ሳሎንዎ የቤትዎ ዋናኛ እንብርት ነው፡፡ ሳሎንዎ የሚዝናኑበት፣ ፈታ የሚሉበት፣ ያልተጨናነቀ ጊዜ የሚያሳልፉበት፣ ከወዳጅ ከቤተሰብ የሚጫወቱበት ምርጡ ቦታም ነው፡፡ ይህን የመሰለ ክፍልዎን ለማስዋብ ለማስጌጥ እና ቆይታዎን ምቹ ለማድረግ የፈርኒቸር ምርጫዎን ማስተካከል ይኖርብዎታል፡፡ የሳሎን የፈርኒቸር መገልገያዎችን በተመለከተ በርካታ አማራጮች አሉ፡፡ ምርጫዎ ምንድን ነው? ሶፋ፣ የቡና ጠረጴዛ፣ የመጻሕፍት መደርደሪያ ለምርጫ ከሚቀርቡ ሳሎናችን ቅንጡ፣ ሳቢና ምቹ ለማድረግ ከምንገለገልባቸው ፈርኒቸሮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ እንምርጫዎ ሌሎች ዓይነት ወንበሮችና እና ነጠላ በርኩማዎችንም ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ ለሳሎንዎ የሚያገለግሉ መገልገያ ፈርኒቸሮች በሚገዙበት ጊዜ ዘወትር ሊያተኩሩ የሚገባው ምቾት ላይ ነው፡፡ ደግሞስ ሳሎንዎ ራስዎን የሚሣርፉበት ዘና የሚሉበት አይደለምን? ስለዚህ ለዚሁ ተዝናኖትዎ የሚያገለግሉዎትን ፈርኒቸሮች መሸመት ይኖርብዎታል፡፡ ከፍተኛ ጥራት ካላቸው ጥሬ ዕቃዎች የተሰሩትን፣ ለወገብዎና እና ለራስዎ በቂ ድጋፍ የሚሠጡዎትን ሶፋዎች ይሸምቱ፡፡ ሌላው ለሳሎንዎ የሚሆኑ የመገልገያ ፈርኒቸሮችን በሚሸምቱበት ጊዜ ሊያተኩሩበት የሚገባው ነጥብ ቅንጡነት( ስታይል) ይባላል፡፡ የቤትዎ መገልገያዎች የእርስዎን የቀለም እና የቅርጽ ምርጫ እና የዘመናዊነት አረዳድ የሚያሳዩ መሆን አለባቸው፡፡ ምርጫዎ ዘመናዊ ባህላዊ፣ ክላሲክ ይሁን ሌላ ማንኛውም ቢሆን ዘወትር አማራጮች አያጡም፡፡ ደግሞስ ዋናው ቁምነገር የእርስዎን ምርጫ እና ምቾት የሚያሟሉ ፈርኒቸሮች ማግኘት አይደለምን? እናም ከምናቀርባቸው በርካታ ዓይነት የፈርኒቸር መገልገያዎች ለእርስዎ የሚሆን እኛ ዘንድ ማግኘት እንደሚችሉ እናረጋግጥልዎታለን፡፡ በባለሙያ ዓይን ምርጫዎን በማጉላትም እናግዝዎታለን፡፡ ይምጡ! ይጎብኙን